የቪዲዮ ትምህርቶች ለማግኘት ከላይ ያሉትን ሊንኮች ይምረጡ - Video tutorials will be posted in each category
የቪዲዮ ትምህርቶች ለማግኘት ከላይ ያሉትን ሊንኮች ይምረጡ - Video tutorials will be posted in each category
Sutueal Bekele
Based in Melbourne, Australia. A cross-platform 3D modeler, animator and visual effects artist and Fine art.
BA: 3D Animation and Visual Effects; Dip: Screen and Media; Other: Visual Art Studies
ዲዛይ ኢትዮ.ኮም በዓለም እጅግ እውቅ የሆኑ የኢንተርቴይመንት ኢንዱስትሪ 3-ዲ ሞዴሊንግ፣ አኒሜሽን፣ ጌም ዲዛይን እና ቪዥዋል ኢፌክት ኮምፒውተር ሶፍትዌሮችን ከኢትዮጵያውያን እንዲሁም አፍሪካውያን ወጣቶች ጋር ክህሎቶችን ለመለዋወጥ የሚሰራ ድረ-ገጽ ነው። የእነዚህን ኮምፒውተር ፕሮግራሞች ሙያ ያላቸው ማናቸውም ባለሙያዎች ወይንም ድርጅቶች አብረን እንድንሰራ በትህትና ተጋብዛችኋል።
Design Ethio.com is a website dedicated to knowledge sharing on the latest 3D modeling, animation, game design, and visual effects software in Africa. Our current video tutorials are in Amharic, one of the Ethiopian languages. If you are a 3D modeler, 3D animator, 2D animator, digital artist, VFX artist, game designer, or programmer and would like to share your knowledge in any native African language, we would love to work with you.
ማያ የ3-ዲ ሞዴሊንግ፣ አኒሜሽን እንዲሁም ቪዥዋል ኢፌክት ለመፍጠር የሚያገለግል የ3-ዲ ኮምፒውተር ግራፊክስ ፕሮግራም ነው። በማያ ማንኛውንም አይነት ለፊልም የሚሆን ገጸ ባህሪ እንዲሁም አካባቢ መፍጠር ይችላል። ቪዥዋል ኢፌክት እንዲሁም ቨርችዋል ሪያሊቲ ለመስራት ሲያስችል በአለም ካሉት ትልልቅ ታዋቂ የአንሜሽን ፊልሞች የተሰራበት ሲሆን፣ ለቴሌቭዥን አንሜሽን ፕሮግራሞችና አድቨርታይዝምንቶች ተመራጭ ሶፍትዌር ነው።
ሰብስታስ ፔንተር የ 3-ዲ ሞዴሎችን ማንኛውንም የረቀቁ ቀለማትን፣ ለስላሳነትና ሸካራነት እንዲያሳዩ ማድረግ የሚያስችል ሶፍትዌር ነው። እ.አ.አ ከ 2014 ገና ከመጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ3-ዲ ዲጂታል የሥዕል ፕሮግራም በመሆን ለአኒሜሽን እንዲሁም ለጌም ኢንዱስትሪ እውቅናን በማትረፉ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ብቸኛው የ3-ዲ ዲጂታል የሥዕል መማሪያ ፕሮግራም መሆን የታወቀ ነው። በዚህ ሰአት ሶፍትዌሩ በአዶቢ (Adobe) ትገዝቶ ዋጋው ቢያሻቅብም አሁንም ተተኪ ያላገኘ የ3-ዲ ዲጂታል የሥዕል ሶፍትዌር ነው።
አንሪል ኢንጅን በዓለም ዙሪያ በጌም ዲዛይን አሉ ከሚባሉት ሁለት ትላልቅ ሶፍትዌሮች አንዱ ነው። የጌም ዲዛይን ካምፓኒዎችና ቡድኖች ከሚጠቀሙባቸው በጣም ተወዳጁ ሲሆን የአሁኑ እትም UE5 ቴክኖሎጂው ለቀጣይ ትውልድ ለጌም ዲዛይን ብቻ ሳይሆን በበርካታ ኢንዱስትሪዎች ተወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ የቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት፣ በፊልም ባክግራውንድ ሴታፕ፣ የኮንሰርቶች የቀጥታ ስርጭት ላይ እጅግ አስግራሚ ቨርችዋል አለምን ለማሳየት እየዋለ ሲሆን በሰፊ ኢንዱስትሪዎች ተመራጭነቱ እጅግ ልቋል።
ማሪ፣ የሰብስታስ ፔንተር (Substance Painter) አይነት የ3-ዲ ሞዴሎችን ስዕል ያለ ገደብና ውስብስብ የሆኑትን ገፅታዎችን በመስራት በአንሜሽን ፊልም እንዲሁም በጌም ኢንዱስትሪ በአርቲስቶች ተመራጭ የ3-ዲ መሳርያዎችን (Tools) በማቀናጀት የፈለጉትን መልክ እንዲፈጥሩ ማድረግ ሲያስችል ፣ ይህም ሰፋፊ ዲዛይኖችን ፣ የተወሳሰቡ ከፍተኛ መጠን ያላቸውን ዲዛርይኖችን በቀላሉ በማለያየት የፈጠራን ስራ ልዩ እንዲሆን ማድረግ ቢያስችልም ፣ ትንሽም ቢሆን ቀደም ያለ የስዕል እውቀት ያላቸው ብዙ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።
ማርቨለስ ዲዛይነር የ3-ዲ ልብሶችን እንዲሁም የጨርቅ አይነቶችን ለመፍጠር የሚያስችል የዲጂታል ግራፊክስ (Cloth Simulation) አለምአቀፍ መሪ ነው።
ማርቨለስ ዲዛይነር ለጌም ፣ ለቪኤፍ ኤክስ፣ ለልብስ ዲዛይነሮች እና በሌሎች ኢንዱስትሪዎች የ3-ዲ ምናባዊ ልብስን ለመፍጠር የኢንዱስትሪ ተመራጭ ሲሆን ፣
እጅግ በጣም አስደናቂ የመፍጠር አቅምን በሚያበረታ ቴክኖሎጂ የታገዘ በመሆኑ፣ ልብስ መንደፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሰው በ3-ዲ በተሰሩ ሞዴሎችም ላይ በቀላሉ የራስን ንድፍ በመፍጠር ቀላል ፣ ፈጣን ፣ አስደናቂ ውጤቶች ያስገኛል።
ዚብረሽ ለዲጂታል ቅርፃቅርፅ እና ስዕል ነክ የ3-ዲ ኢንዱስትሪ ደረጃውን የጠበቀ እጅግ ፈጣንና ምናባዊ ሸክላ አይነት ቅርፆችን ለመስራት የሚያስችል ሲሆን፣ በቀላሉ ለመቅረጽ የሚያስችሉ ብሩሾችን እንድንትጠቀም ይረዳል።
ዚብረሽን እጅግ የታወቁ የፊልም ስቱዲዮዎች፣ የጌም ስቱዲዮዎች፣ በአንሜሽን ሰሪዎች፣ ጌጣጌጥ ዲዛይነሮች፣ አውቶሞቲቭና አቪዬሽን ዲዛይነሮች፣ ሳይንቲስቶች እና ሌሎች በዓለም ዙሪያ ባሉ ባለሙያዎች እንዲሁም አርቲስቶች እጅግ ተወዳጅ ነው።
ዚብረሽ የቴክኖሎጂ አካዳሚ ሽልማት ያገኘ ሲሆን ለፊልሞች፣ ለቪዲዮ ጌሞች ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን 3-ዲ ሞዴሎችን ለመፍጠር ጥቅም ላይ ስለሚውል በበርካታ ዲዛርን ዩኒቨሪስቲዌችና ኮሌጆች የዚህ ሶፍትዌር ትምህርት ይሰጣሉ።
coming Soon
coming Soon
We use industry standards computer program such as Maya, substance painter, zbrush, marvelous designer, mari, mudbox, houdini, unreal engine, e-on software vue, adobe creative suite and others.
Let us know if you have any project. We will be happy to work with you.
Copyright © 2024 design ethio - All Rights Reserved.
Powered by design ethio
We use cookies to analyze website traffic and optimize your website experience. By accepting our use of cookies, your data will be aggregated with all other user data.